ለኮሮናቫይረስ ክትባት ማፈላለግ ስራ የሚደረጉ ድጋፎች እንዲጠናከሩ የዓለም ጤና ድርጅት ጥሪ አቀረበ

Category : News | Posted on 2020-05-29 09:32:17


ለኮሮናቫይረስ ክትባት ማፈላለግ ስራ የሚደረጉ ድጋፎች እንዲጠናከሩ የዓለም ጤና ድርጅት ጥሪ አቀረበ

ለኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት የማፈላለግ ስራውን ለማፋጠን የሚደረጉ ድጋፎች እንዲጠናከሩ የዓለም ጤና ድርጅት ጥሪ አቀረበ።

ከ7 እስከ 8 የሚሆኑ የተለያዩ አይነት ክትባቶች ተመርጠው እየተሰራባቸው መሆኑንም የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አስታውቅዋል።

የክትባቶቹን አይነት ይፋ ያላደረጉት ዶክተር ቴድሮስ፥ ከ100 በላይ የክትባት አይተነቶች እንደቀረቡና ከእነዚህም ውስጥ የተሻሉ እና ውጤታማ ይሆናሉ ተብሎ የታመነባቸው ከ7 እስከ 8 የሚሆኑ ተመርጠው እየተሰራባቸው ነው ብለዋል።

ክትባት የማበልፀግ ስራው ላይም ከ400 በላይ ተመራማሪዎች በመሳተፍ ላይ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።

Contact Us

Sign Up For Our News Letters

Connect With Us

Phone :+251 11870 3889

Email : [email protected]

Address : Addis Ababa, Bekilo Bet

© 2020 Ethiopian Association of Anesthetist . All Rights Reserved | Developed by Ase Abe