የኢትዮጵያ አንስቴቲስቶች ማህበር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ

የኢትዮጵያ አንስቴቲስቶች ማህበር ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በቢሾፍቱ ዳካ ሆቴል ተካሄደ፡፡በጉባኤው ላይ የጉባኤው አባላት እና የማህበሩ የክልል ተወካዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን፡ የማህበሩን የ2014 ዓ.ም አመታዊ ሒሳብ የውጪ ኦዲት ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፡ ማህበሩን በአዲስ መልክ ማዋቀርን በተመለከተ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው መነሻ ሀሳብ በማውረብ በጉባኤው የተገኙ አባላት ሰፊ ውይይት ከተደረገበት በኋላ አሁን ላይ ያለውን የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ቁጥር ከ 51 ወደ 53 በማሳደግ በየክልሉ የአንስቴቲስቶችን ብዛት ከግምት ውስጥ በማስገባት ለሁሉም ክልሎች የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ኮታ የተወሰነላቸው ሲሆን በቅርብ አጠቃላይ 15ኛው ኮንፈረንስ ተጠርቶ በተመደበው ኮታ መሰረት የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ምርጫ ተከናውኖ ከተመረጡት የጠቅላላ ጉባኤ አባላት መካከል ደግሞ የማህበሩ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴን በመምረጥ በአዲስ መልክ ማህበሩን ለማጠናከር ውሳኔ ተላልፎበታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ማህበሩ በአዲስ መልክ ያሰራውን የአባላት ዳታቤዝ (Membership Management System) እነዲሁም የኢለርኒንግ ሲስተም(online Learning management system) ያስተዋወቀ ሲሆን ከዚህ በፊት አባል የሆኑም ሆነ ያልሆኑም በሁለቱም ሲስተሞች ላይ መመዝገብ እንዳለባቸው ጥሪ ቀርቧል፡፡

%d bloggers like this: